Tuesday, November 21, 2017

ሰው በኃይሉ አይበረታምና

የዮሐንስ ወንጌል 1:46
//ፊልጶስ ናትናኤልን አግኝቶ፦ ሙሴ በሕግ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን አግኝተነዋል አለው። ናትናኤልም፦ ከናዝሬት መልካም ነገር ሊወጣ ይችላልን? አለው። ፊልጶስ፦ መጥተህ እይ አለው።//
ፍልጶስና ንትናኤል የመጽሃፍት አዋቂና አጥኒ ሳይሆኑ አይቀርም ኦሪትን ጠንቅቀው የሚያቁ ነብያትን መጽሃፍት አበጥረው ያጠኑ ለዛ ነው ጌታ ፍሊጶስን ተከተለኝ ብሎት ከጌታ ጋር ካሳለፈው ጥቂት ጊዜ ተነስቶ በእውነትም ሙሴ በኦሪት ነቢያትም በትንቢት የተናገሩለት መሲሁ እየሱስ በእርግጥ እሱ እንደሆነ እርግጠኛ ሆኖ ለጋደኛው ለናትናኤል የናዝሬቱ ኢየሱስን አግኝተነዋል ብሎ የነገረው(የሚገርመው ኢየሱስ እራሱ ነው ያገኘው እንጂ ያነበበው የኦሪት ወይም የነብያት መጽሃፍ መሲሁ ማን ነው ወይም መቼ ነው የሚመጣው የሚለውን ጥያቄ ቢያጭርባቸውም ቅሉ....ኢየሱስ ግን እራሱ ፈልጎ አገኛቸው) ...ከሁለቱ ግን የሚገርመኝ ናትናእኤል ነው እንደዛ የመጽሃፍት እውቀት እና ጥማት ትጋት ኖሮት.....ለእግዚሃብሄር መንግስት መስፋት ወይም አሁን ላለነው ክርስቶያን የሚጠቅም ስራ ስላልሰራ መጽሃፍ ቅዱስ ላይ ጉልህ ታሪክ አልተቀመጠለትም.....ከሱ ይልቅ አንድ ሃጥያተኛ ሳምራዊት በአይሁድ ማህበረሰብ የምትናቅ የሃጥያተኞች ወዳጅ ለተናቀው አክባሪ ኢየሱስ ቀርቦ ጉዷን ሲነግራት ይመጣል የተባለው መሲህ እሱ እራሱ እንደሆነ ሲገልጽላት ለአንድ ሰው አደለም ሄዳ የተናገረችው ከተማውን አሰልፋ ነው ያመጣችው የሚገርም ነው ይህች ምስኪን ስሟን በመጽሃፍ ቅዱስ በደማቁ ተጽፎላት አለፈች....እግዚሃብሄር ጠቢባንን ያሳፍር ዘንድ በደካሞች በተናቁት ይሰራል.... አንዳንዴ ክርስትና ይቀልብናል ልክ ፍልጶስ እንዳለው የናዝሬቱን ኢየሱስን "አግኝተነዋል" ማለት ይዳዳናል በእኛ እውቀት መጽሃፍ ቅዱስ አንብበን የሃንስ 3:16 ገብቶ እና ተገርመን እውነትም አዎ እኢየሱስ ያድናልል በለን እንደመጣን ነው የምንመጻደቀው...አደለም ዩሃንስ 3:16 ሙሉ መጽሃፍ ቅዱሱን የሚያሰምሩ የዩንቨርሲቲ ፕሮፌሰሮች እኢየሱስን አላገኙትም አላመኑትም እውቀት አያድንም ሰው በሃይሉ አይበረታምና....ግን እንዲያው በነጻ የማይገባን ሆነን ሳለ ነው በምህረቱ ብዛት የዳነው...እንዲያውውውውው.....

 ሃና እንደዚ አለች ============================
ሳሙኤል ቀዳማዊ 2:3-7
 አትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር አይውጣ። የኃያላንን ቀስት ሰብሮአል፥ ደካሞችንም በኃይል ታጥቀዋል። ጠግበው የነበሩ እንጀራ አጡ፤ ተርበው የነበሩ ከራብ ዐርፈዋል፤ መካኒቱ ሰባት ወልዳለችና፥ ብዙም የወለደችው ደክማለች። እግዚአብሔር ይገድላል ያድናልም፤ ወደ ሲኦል ያወርዳል፥ ያወጣል። እግዚአብሔር ድሀ ያደርጋል፥ ባለጠጋም ያደርጋል፤ ያዋርዳል፥ ደግሞም ከፍ ከፍ ያደርጋል። ======================================

No comments:

Post a Comment