Tuesday, November 21, 2017

መሪ(Leader) ወይስ ካድሬ


አንድ ፖለቲከኛ ካድሬ ወይም መሪ መሆኑም ለማወቅ ቀላል ዘዴዎች:
1.ሁሉንም የስሜት ህዋሳት(በግልጽ ከሚታዩት በተጨማሪ ህልም ማለም, ቪዥዋሊዘ ማድረግ እና ኮመን ሴንስ) የሚጠቀም ከሆነ እሱ/ሷ መሪ ናት/ው:: ካድሬዎች ውስን የስሜት ህዋስን በቻ ነው መጠቀም የሚችለው እንደበቀቀን መድገም ወይም አድርግ የተባለውን ማድረግ ወይም አጠገቡ ያሉት ብዙሃኑ የሚያደርጉትን ማድረግ ::

 2.መሪ የራሱ ቋንቋ አለው ተራ የሆነ ህዝብ የሚያሰለች ጀነሪክ የሆነ ቃል አያበዛም::ካሪዝማ ሞገስ አለው ሰው በቀላሉ ጆሮ ይሰጠዋል ይከበራል:: ካድሬ በራሱ ማሰብ ና አናላይዝ ማድረግ ስለማይች የሚጠቀመው ቃል አሰልቺ የተሸፋፈነ በቃላት ውስጥ ለመደበቅ የሚያስችል.. ለምሳሌ የወያኔ ካድሬ የሆነ ሰው ሁሉ የሚደጋግመው ቃል (ትህምክት ጠባብ ጸረ ህዝብ አቆርቋዥ በኩርኩም ነበር እራሱን ማቅርቆዝ),,,,,አገራችን እየተከተለች ባለችው አቢዮታዊ ዲሞክራሲ,,,,,,,እኝ እኝኝኝ እንቅልፍ ,,,,,,በተከታታይ በተመዘገበው የ11 በምቶ እድገት....አዝግ............ብሄር ብሄሮች ዲሞክራሲያዊ መብታቸው ተከብሮ,,,,

3. መሪ ችግሮችን የሚፈታው ትክክለኛ ጥናት በባለሙያዎች በማስጠናት ያንን ባለሙያዎች ያቀረቡትን የመፍትሄ ሃሳብ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል መዋቀር መዘርጋትና መዋቅሩን የሚመሩ ተጨማሪ መሪዎችን በቦታው በመመደብ እና የሚፈለገው ለውጥ ካልመጣ በጀመሪያ ከስሩ ያሉትን መሪዎች ተጠያቂ ማድረግ ከፍ ሲልም በግልጽ እራስን ተጠያቂ አድርጎ ከሃላፊነት ማንሳት:: ካድሬ ችግሮችን የሚፈታው በስብሰባ ብዛትና ስብሰባው ላይ የራሱን ሃሳብ ሌሎች አነስተኛ ካድሬዎች ቃል በቃል የሱን ሃሳብ ማነብነብ እስኪችሉ ድረስ የስብሰባ ማራቶን ማድረግ:: . . .

No comments:

Post a Comment