Saturday, December 9, 2017

መንፈስ ቅዱስ

መንፈስ ቅዱስ
ነገስት 6:34

የእግዚአብሔርም መንፈስ በጌዴዎን ገባበት፥ እርሱም ቀንደ መለከቱን ነፋ፤ የአቢዔዝርም ሰዎች ተጠርተው በኋላው ተከተሉት
ወደ ምናሴም ነገድ ሁሉ መልክተኞችን ሰደደ፤ እነርሱም ደግሞ ተጠርተው በኋላው ተከተሉት፤ መልክተኞችንም ወደ አሴርና ወደ ዛብሎን ወደ ንፍታሌምም ሰደደ፥ እነርሱም ሊገናኙአቸው ወጡ።
ይህ ከወገኑ ከሁሉ ይልቅ የተጠቃ(ምናሴ) ከቤተሰቡ የሁሉ ታናሽ የ እለት ስራውን እርሻውን እራሱ ተደብቆ በፍርሃት የሚሰራ ሰው.....የንግስና ዘር ከነገዱ የሌለ ስለ ጦር አመራር የማያውቅ ተራ ገበሬ እንዴት...የአቢዔዝር ሰዎች የምናሴም ነገድ ሰውች የአሴር የዛብሎን ና የንፍታሌም ሰዎች ሁሉ ከኋላው ማስከተል እንዴት ቻለ
እግዚሃብሄር እራሱ ተገልጦለት አንተ ጽኑ ሃያል ሰው ብሎት እንኳ የአባቱን የሰፈሩን የበአል መሰዊያ ለማፍረስ ከፍርሃቱ እተነሳ በሌሊት ሰው እንዳያየው ተደብቆ ነበር ያፈረሰው
የሚገርመው የሰፈሩ ሰዎች ሊገሉት ሲመጡ እራሱን እና ድርጊቱ ለመከላከል በክርክርም ለማሳመን ስለፈራ ተደብቆ እያለ የተሟገተለት የበአል አምላኪ የሆነው የበአል መሰዊያው ባለቤት አባቱ(ኢዩአስ) ነበር::ስለ እግዚሃብሄር ሃያልነት ብርታት እግዚሃብሄር የተገለጠለት እያለ ጣኦት አምላኪ የተሻለ መልስ የተሻለ ተሟጋች ሲሆን አይገርምም

ሃዋርያትን እራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ በተግባር;አብሮ በመጸለይ;ለብቻውም በመጸለይ; በሚታይ ህይወት ;በቃል;በምሳሌ ;በስልጣን ;በድንቅ ;በምልክቶች ከ3 አመት በላይ አስተምሯቸው የጭንቅ ጊዜ ሲመጣ አፈገፈጉ በተለይም ጴጥሮስ እነዚህ ሁሉ ቢክዱ አብሬህ እስከ መጨረሻው አልለይህም ያለው በአንድ ተራ ሰው ፊት አላቀውም አለ::
//ዩሃ 16:12
የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፥ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም።
ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።
እርሱ ያከብረኛል፥ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋልና።
//
ይሄ የ እውነት መንፈስ ይሄ አጽናኝ ይሄ ሃይል በመጣና በነካው ጊዜ ጊዜ ግን ጴጥሮስ አይደለም በአንድ ባልተማረች ገረድ ፊት እንዳልተርበተበተ ከአለም ዙሪያ ከመጡ የተለያየ እውቀትና የተለያየ ቋንቋ ባላቸው ሰዎች ፊት ለፊት ቆሞ በድፍረት ስለ እኢየሱስ ለመናገር ደፈረ ሃይል አገኘ ጥበብ አገኘ ሞገስ አገኘ መደመጥ አገኘ መፈራት አገኘ....
ወደ ጌዲዮን ስንመለስ ተመሳሳይ ነገር ነው የሆነው እስራኤልን እንዲታደግ ተመርጦ እግዚሃብሄር አንተ ጽኑ ሃያል ሰው ብሎ ያደፋፈረው የተናገርው ነገር ግን በሰፈሩ በቤቱ የእግዚሃብሄርን ስራ ለመስራት ለመናገር ሲፈራ ሲደበቅ የምናየው ጌዲዮን የእግዚሃብሄር መንፈስ ሲገባበት ግን ልዩ ሰው ሆነ በአደባባይ መውጣት ደፈረ ቀንደ-መለከት አነሳ እንደ ንጉስ አገርን ለመታደግ አገራዊ ጥሪ ለማወጅ ተነሳ መለከት ነፋ ከሁሉ ታናሽ የነበረው በእግዚሃብሄር መንፈስ ከሁሉ ቀዳሚ መሪ ታዳጊ ሆኖ የአቢዔዝር ሰዎች የምናሴም ነገድ ሰውች የአሴር የዛብሎን ና የንፍታሌም ሰዎች እነዚህን ሁሉ ከኋላው ማሰለፍ ቻለ::


የእግዚሃብሄርን የመንግስቱን ወንጌል ለአንድ ለተራ ሰው እንኳ ማድረስ አይቻልም በራሳችን እውቀት ጥበብ አይደለም ለሌላ ሰው እኛም ትላንት በተገለጸልን እውቀት መዳን ብርሃን መጽናት አንችልም ሃዋሪያቱ አልቻሉም ጴጥሮስ ህያው ምስክር ነው ነገር ግን የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ከራሳችን ተርፈን ለጎረቤት ለአለም መትረፍ ሰዎችን ሁሉ ከኋላችን ማሰለፍ ሞገስ ጥበብ ሃይል ይሆንልናል ይበዛልናል::


መገኘትህን አትውሰድብኝ ......ያለው ዳዊት ምንኛ መንፈስ ቅዱስ ከእስትንፋስ ይልቅ የሚቀርብ እንደሆነ የገባው የተረዳ ከሚተነፍሰው አየር የበለጠ አስፈላጊ እንደሆነ የተረዳ .........በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበረ ነገር ግን ከባለአምሳ በኋላ እንዳለው ዘመን እንደኖሩት እንደ አዲስ ኪዳን ኑሮ የኖረ የሚገርም ዳዊት

No comments:

Post a Comment