Sunday, December 24, 2017

"Christmas"/ገና/የኢየሱስን ክርስቶስ ልደት ላንተ ምንድነው??

       
//መጽሐፈ አስቴር 9:21-22
በየዓመቱም አዳር በሚባለው ወር አሥራ አራተኛውና አሥራ አምስተኛው ቀን፥
አይሁድ ከጠላቶቻቸው ዕረፍትን ያገኙበት ቀን፥ ወሩም ከኀዘን ወደ ደስታ ከልቅሶም ወደ መልካም ቀን የተለወጠበት ወር ሆኖ ይጠብቁት ዘንድ፥ የግብዣና የደስታም ቀንእርስ በርሳቸውም ስጦታ የሚሰጣጡበትና ለድሆች ስጦታ የሚሰጡበት ቀን ያደርጉት ዘንድ አዘዛቸው።//


[26 ስለዚህም እነዚህ ቀኖች እንደ ፉር ስም ፉሪም ተባሉ] በአስቴርና በ እነ መርዶኪዎስ ዘመን የነበሩ አይሁዳውያን የፉሪም በአል ምንድነው ብለን ብንጠይቃቸው
የሚሉት ብዙ አላቸው.....እንደ ሜዶንና እንደፋርስ የጸና የንጉስ አዋጅ የሞት አዋጅ ታውጆባቸው ሳለ እግዚሃብሄር የተመረጠ ህዝቡን ለማዳን ለአስቴርና መርዶኪዎስ
በኩል ሞገስ ሆናቸው ህዝቡን ለማዳን ንጉሱ ያወጣውን ህግ አላሻረም የሞት አዋጅ እንደታወጀ ህጉ ሳይሻር ይልቁኑ ለየት ያለ የተሻለ ነገር ሆነ ይኽውም
የአይሁድ ህዝብ ሁሉ እራሱን መከላከል እንዲሁም ጠላቱን ማጥፋት የሚያስችል መብት የሚያጎናጽፍ ህግ ወጣ በየአውራጃውም እስከ ግዛቱ መጨረሻ ታወጀ


//መጽሐፈ አስቴር 8:11-13
በዚያም ደብዳቤ በከተሞቹ ሁሉ የሚኖሩት አይሁድ እንዲሰበሰቡ፥ ለሕይወታቸውም እንዲቆሙ፥ በጥል የሚነሡባቸውን የሕዝቡንና የአገሩን ሠራዊት ሁሉ ከሕፃናቶቻቸውና ከሴቶቻቸው ጋር እንዲያጠፉና እንዲገድሉ እንዲደመስሱም፥ ምርኮአቸውንም እንዲዘርፉ ንጉሡ ፈቀደላቸው።
ይህም አዳር በሚባለው በአሥራ ሁለተኛው ወር በአሥራ ሦስተኛው ቀን በንጉሡ በአርጤክስስ አገሮች ሁሉ በአንድ ቀን እንዲሆን ነው።
አይሁድም ጠላቶቻቸውን እንዲበቀሉ በዚያ ቀን ይዘጋጁ ዘንድ የደብዳቤው ቅጅ በየአገሩ ላሉ አሕዛብ ሁሉ ታወጀ።//


በአዲስ ኪዳን ለኛ የሆነው ግን ለየት ይላል.........በአዳም ሃጥያት/አለመታዘዝ ሞት ወደ አለም እንደገባ እናም የዚህ የሞት አዋጅ ሰለባዎች ሆነን ሳለ ....የሙሴ ህግ
ከሃጥያት ከሞት አላዳነንም ወይም ለነአስቴር እንደሆነው የተሻለ ህግ እራስን መከላከል የሚያስችል አዋጅ አልታወጀም ምክንያቱም ሃጥያትም መከላከል በስጋ አይቻልም ህግን በመጠበቅ መጽደቅ አልተቻለም ይልቁንም ህግ የባሰውኑ ሃጥያተኛ እንደሆንን ብቻ ነው የሚነግረ.....ይልቁኑ እግዚሃብሄር ወልድ መድሃኒያለም ሆኖ
እራሱን ለ እኛ ለመስጠት ህይወቱን ስለ ሃጥያታችን ቅጣት ሞት የኛን ሞት ለመሞት ሰው ሆኖ ወደ ምድር መጣ ...............ስለዚህ የክርስቶስ ልደት አመት በአል ወይም ሆሊ ደይ አይደለም............የጠፋውን የሰው ልጅ ለማዳን ክርስቶስ ክብሩን ትቶ እንደ ሰው ሆኖ ለአዳም ዘር ለመሞት ፈቃደኛ ሆኖ ወደ ምድር መጥቶ ከድንግል ማርያም የተወለደበት ቀን ነው.........


//የዮሐንስ ወንጌል 8:3-5
ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዘችን ሴት ወደ እርሱ አመጡ በመካከልም እርሱዋን አቁመው፦
መምህር ሆይ፥ ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች።
ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ? አሉት።//

ይቺ ስታመነዝር የተያዘችው እየሱስ ከሞት ያስመለጣት ሴት ዛሬ ብትኖር የኢየሱስን ልደት እንዴት ታከብረው ይሆን??

//የማቴዎስ ወንጌል 8:28
ወደ ማዶም ወደ ጌርጋሴኖን አገር በመጣ ጊዜ፥ አጋንንት ያደሩባቸው ሁለት ሰዎች ከመቃብር ወጥተው ተገናኙት፤ እነርሱም ሰው በዚያ መንገድ ማለፍ እስኪሳነው ድረስ እጅግ ክፉዎች ነበሩ።//


በአጋንንት እስራት ተይዘው የነበሩት እነዚህ ሰዎች በዚህ ዘመን ቢኖሩ የክርስቶስን ልደት እንዴት ያከብሩ ነበር???



እናንተ የኢየሱስን ልደት እንዴት እያከበራችሁት ነው?????



//ትንቢተ ኢሳይያስ 9:2
በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው።//




No comments:

Post a Comment