Friday, December 15, 2017

የእግዚሃብሄርን ጦርነት ብቻ ተዋጋ


  12/15/2017  0400

//1 ሳሙኤል 29:8-9
ዳዊትም አንኩስን፦ ምን አድርጌአለሁ? ሄጄስ ከጌታዬ ከንጉሡ ጠላቶች ጋር እንዳልዋጋ፥ በፊትህ ከተቀመጥሁ ጀምሬ እስከ ዛሬ ድረስ በእኔ በባሪያህ ምን አግኝተህብኛል? አለው።
አንኩስም መልሶ ዳዊትን፦ እንደ አምላክ መልእክተኛ በዓይኔ ፊት መልካም እንደ ሆንህ አውቃለሁ፤ ነገር ግን የፍልስጥኤማውያን አለቆች፦ ከእኛ ጋር ወደ ሰልፍ አይወጣም አሉ።አሁንም አንተ ከአንተም ጋር የመጡ የጌታህ ባሪያዎች ማልዳችሁ ተነሡ፤ ሲነጋም ተነሥታችሁ ሂዱ አለው።//

ዳዊት ከ ሳኦል ማሳደድ ለማምለጥ ወደ ፍልስጤማውያን ምድር በመሄድ አንኩስ የተባለው የጌት ንጉስ መኖሪያ ሰጥቶት ዳዊትና አብረውት ያሉት 600 ተከታዮቹ/ሰራዊት ለ 1 አመት ከ 4 ወር ኖረዋል::

ፍልስጤማውያን እስራእኤላውያን ለመውጋት በሚዘጋጁበት ጊዜ ዳዊትም አብሯቸው ለመዋጋት እንዲወጣ ንጉስ አንኩስን ሲጠይቅ ይታያል
ዳዊት እስራእኤላውያን ከዚህ በፊት ወደጦርነት ከመውጣታቸው በፊት እግዚሃብሄርን እንደሚጠይቁት በእግዚሃብሄር ፊት ሆኖ ስለጦርነቱ አብሯቸው መውጣት አለመውጣ እንዳለበት አልጠየቀም ይልቁንም በስጋዊ አስተሳሰብ ምናልባትም የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው በሚል አስተሳሰብ ሌሎች አረማውያን እንደሚያደርጉት በማሰብ የራሱን ወገኖች በምውጋት ታሪካዊ ስህተት ለመስራት ሲዘጋጅ እናያለን:: እግዚሃብሄር ግን የምህረት አምላክ ስለሆነ ዳዊት እንዳሰበው አልሆነም የፍልስጤማውያን አለቆች ከጠላታቸው ጋር ወግኖ ይወጋናል  ብለው ፈርተው አብሯቸው እንዳይወጣ ከለከሉት::

ስንት ግዜ በስጋዊ አስተሳሰብ በመነዳት የእግዚሃብሄርን ወገን በድዬ ይሆን እግዚሃብሄ ምህረቱን ይላክልኝ በእግዚሃብሄር ፊት ሆነን ያልተቀበልነው ምሪት ሆነ ስራ በስጋ ያሰብነው አብዛኝው ከውጤታማነቱ ይልቅ የሚያስከትለው ኮላቶራል ዳሜጅ ከፍተኛ ነው::በተለይ በህይወቴ በኢትዮጲያን የፖለቲካ ትኩሳት ምክንያት እንዲሁም ጌታን ከማያውቁ ሰዎች ጋር ከሚፈጠረው ጉንጭ አልፋ ክርክር እንዲሁም በመሳሰሉት መንፈስን በማጥፋት ከከፍታዬ ወርጄ ብዙ ግዜ የራሴን የስጋ ጦርነት ስዋጋ አገኘዋለሁ ...

ይህ ሁሉ የሚሆነው ተዘናግቶ በመቀመጥ በስንፍና ጠላት ዲያቢሎስ ሁልጊዜ እኛን እንደሚዞር ቀዳዳ ምክንያት እንደሚፈልግ ካለማስተዋል ነው::

እግዚሃብሄር ዳዊትን ወደ ትራክ ለመመለስ ታሪካዊ ስህተት ያለበት የተሳሳተ ጦርነት እንዳይሄድ ከከለከለው በኋላ ትክክለኛ አሳይመንት የቤት ስራ ሰጠው
የእግዚሃብሄር አላማ የህዝቡ ጠላቶች አማሌቃውያን ፈጽመው እንዲጠፊ ነው  ስለሆነም ዳዊት ፍልስጤማውያን አብሯቸው እንዳይወጣ ከከለከሉት በኋላ ወደ ሰፈር ሲመለስ አማሌቃውያን ጺቅላን ወግተው አቃጥለው በዛ የቀሩትም ምስቶቻቸውን እና ሽማግሌዎችን ማርከው ወስደዋል በዚህ ጊዜ እንደባለፈው እግዚሃብሄርን ሳይጠይቅ በፍጥነት አልወሰነም ምንም እንኳ የገዛ ሚስቶቹ እራሱ ቢማረኩም ከተማዋ እየነደደች ብትሆንም እጅግ አሳዛኝ ሁኔታ ቢሆንም አብረውት የነበሩት ሊወግሩት እስኪመካከሩ ድረስ የነገሩ ሁኔታ አስጨናቂ ቢሆንም   በስጋዊ ቁጣ ንዴት በደም ፍላት እየሮጠው ወደ ውግያ አልወጣም ይልቁንም
መጽሃፉ የሚለው **1ሳሙ30:6 ...ዳዊት ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ልቡን አበረታ።**.... ወደ እግዚሃብሄር በመቅረብም ልከተላቸውን ልውጣን ብሎ ጠየቀ እግዚሃብሄርም አብሮት ወጣ ምርኮም ሰጠው::
የእግዚሃንሄርን ጦርነት ተዋጋ እግዚሃብሄርም ድልን ሰጠው::



No comments:

Post a Comment